Posts

Showing posts from May, 2018
እምቤተ ክህነት ወመንግሥት ዘኀረይዋ ይእቲኬ ማርያም ድንግል            በዲ/ን ታደለ ሲሳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትኩረት አድርጋ የምታከብራቸው በርካታ የቅዱሳን በዓላት አሉ፡፡ የእመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በዓላትም በቤተ ክርስቲያኗ ሰፊ ቦታ ተሰጥተው የሚከበሩ ናቸው፡፡ ለአብነት ያህልም በየዓመቱ ግንቦት አንድ ቀን የሚከበረውን የቅድስት ድንግል ማርያምን የልደት በዓል መመልከት ይቻላል፡፡ ለሃይማኖታችን መሠረት፣ ለክርስትናችን ዋስትና፣ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ስንቅ የሆኑት ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያስረዱን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት 1 ቀን በ15 ዓ.ዓ  ቅድመ ልደተ ክርስቶስ መወለዷን እንረዳለን፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲን፣ ቅዱሳት መጻሕፍትና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት የእመቤታችን ልደት መስከረም 10 በማለት ያከብራሉ፡፡ ይህንንም የተኣምረ ማርያም መቅድም « ወቦ እለ ይቤሉ አመ ዐሡሩ ለመስከረም ልደታ፤ መስከረም 10 ቀን ልደቷ ነው የሚሉ አሉ» ይላል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግን በዐዋጅ ግንቦት 1 ቀን ታከብረዋለች፡፡ ወላጆችዋም ኢያቄምና ሐና ይባላሉ፡፡ አባትዋ ኢያቄም ከቤተ ይሁዳ (ከይሁዳ ነገድ) ሲሆን፣ እናትዋ ሐና ከቤተ ሌዊ (ከነገደ ሌዊ) ናት፡፡ የተወለደችበት ሀገርም ናዝሬት ይባላል፡፡        የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግን በዐዋጅ ግንቦት 1 ቀን ታከብረዋለች፡፡ ወላጆችዋም ኢያቄምና ሐና ይባላሉ፡፡ አባትዋ ኢያቄም ከቤተ ይሁዳ (ከይሁዳ ነገድ) ሲሆን፣ እናትዋ ሐና ከቤተ ሌዊ (ከነገደ ሌዊ) ናት፡፡ የ...